ሁለተኛው የአገርህን ዕወቅ የአገር ውሰጥ በረራ ተካሄደ
ጥቅምት 6 ቀን 2006 ዓ.ም.
ትራንስ ኔሽን ኤርዌይስ ኃላ.የተ.የግ.ማ. (ቲ.ኤን.ኤ) እና ሬይንቦ የመኪና ኪራይና አስጐብኚ አገልግሎት ኃላ.የተ.የግ.ማ (ሬይንቦ) በጋራ በመሆን ያዘጋጁት የአገርህን ዕወቅ የጉብኝት ፕሮግራም በስኬት ተጠናቀቀ፡፡
![]() |
![]() |
ተጓዥ ቡድኑ በባህር ዳር አውሮፕላን ማረፊያ | ጉብኝት በቤዛዊት ቤተመንግስት |
በትራንስ ኔሽን ኤርዌይስ ዳሽ ኤይት (Dash 8) አውሮፕላን ከአዲስ አበባ ወደ ባህር ዳር ጉዞ በማድረግ ጥቅምት 2 እና 3 ቀን 2006 ዓ.ም. የተካሄደው ጉብኝት 33 መንገደኞችን ያካተተ ሲሆን፤ የአባይ ፏፏቴን፣ የባህር ዳር ቤዛዊት ቤተመንግሥትን፣ በጣና ሐይቅ ደሴት ላይ የምትገኘውን ዘጌ ኡራ ኪዳነምህረት ቤተክርስቲያንን እንዲሁም በጣና ሐይቅ ላይ በተደረገ የጀልባ ጉዞ የአባይ ወንዝ መፍሰሻ በርን ለመጐብኘት ተችሏል፡፡
![]() |
![]() |
ጉብኝት በአባይ ፏፏቴ | ጉብኝት በኡራ ኪዳነምህረት ቤተክርስትያን |
በዚህ የአገርህን እወቅ የጉብኝት ፕሮግራም በ2004 ዓ.ም. በዓመታዊው የደንበኞች፣ የሠራተኞችና የቤተሰብ በዓል ላይ በሥራቸው ምስጉን ተብለው የተሸለሙ የማኔጅመንት አባል ያልሆኑ ሠራተኞች በዚህ የጉብኝት ፕሮግራም ተጠቃሚ እንዲሆኑ ተደርጓል፡፡
የጉብኝቱ ተሳታፊዎች በቆይታቸው ከዚህ በፊት ያላዩዋቸውን ታሪካዊ ሥፍራዎች፣ ቅርሶችን እንዲሁም የቱሪስት መስህቦችን ማየታቸው እንዳስደሰታቸው ገልፀው፤ በተለይ በቲ.ኤን.ኤ. አስተማማኝና ምቹ የአውሮፕላን ጉዞ አገልግሎቱ እንዲሁም ሬይንቦ የማስጐብኘት ብቃት ባላቸው ባለሙያዎቹ አንድ ላይ በመሆን ባዘጋጁት የጉብኝት ፕሮግራም ተጓዦቹ መደሰታቸውን ተናግረዋል፡፡
በቀጣይም ትራንስ ኔሽን ኤርዌይስ ኃላ.የተ.የግ.ማ. እና ሬይንቦ የመኪና ኪራይና አስጐብኚ አገልግሎት ኃላ.የተ.የግ.ማ. በጋራ በመሆን በአገሪቱ የሚገኙ ልዩ ልዩ የቱሪስት መዳረሻዎችንና ታሪካዊ ሥፍራዎችን የመጐብኘት ፍላጐቱ ያላቸው የህብረተሰብ ክፍሎችን የማጓጓዝና የማስጐብኘት አገልግሎት ለመስጠት መዘጋጀታቸውን ገልፀዋል፡፡