በሚድሮክ ኢትዮጵያ ቴክኖሎጂ ግሩፕ ኩባንያዎች፣ እህትማማችና ተጋባዥ ተቋማት መካከል የሚካሄደው ዓመታዊ የስፖርት ውድድር ተጀመረ
ኅዳር 30 ቀን 2006 ዓ.ም.
ለሦስተኛ ጊዜ የሚካሄደው የሚድሮክ ኢትዮጵያ ቴክኖሎጂ ግሩፕ ኩባንያዎችና የተጋባዥ ተቋማት የወዳጅነት የስፖርት ውድድር እሁድ ኅዳር 29 ቀን 2006 ዓ.ም. ከጠዋቱ ሁለት ሰዓት በመቻሬ ሜዳ ኮርፖሬት ሴንተር ግቢ ሚድሮክ ኢትዮጵያ ቴክኖሎጂ ግሩፕ መቻሬ ከፖልሪዬስ ባደረጉት የእግር ኳስ ግጥሚያ በታላቅ ድምቀት ተጀምሯል፡፡
የሚድሮክ ኢትዮጵያ ቴክኖሎጂ ግሩፕ ቺፍ ኤግዚኪዩቲቭ ኦፊሠር ዶ/ር አረጋ ይርዳው በበዓሉ መክፈቻ ወቅት በየዓመቱ የምናካሂደው ስፖርት ለመሸናነፍ ሳይሆን የክቡር ዶ/ር ሼክ ሙሐመድ ሁሴን አሊ አል አሙዲ ኩባንያዎች አንድነታቸው እንዲጠናከር፣ የእርስ በእርሰ መቀራረብ እንዲፈጥሩና ቤተሰባዊ ትስስራቸው እንዲጐለብት፣ የሥራ መንፈሳቸው የነቃ እንዲሆንና የእኔነት ስሜት እንዲያድርባቸው ለማድረግ የታሰበ ነው ብለዋል፡፡
በውድድሩ ከቴክኖሎጂ ግሩፑ ኩባንያዎች በተጨማሪ ተጋባዥ የሆኑት እህት ኩባንያዎችና የመንግሥት ተቋማት በወዳጅነት መንፈስ በመተያየት ስፖርታዊ ወዳጅነትን እንዲያጠናክሩ ዶ/ር አረጋ አሳስበዋል፡፡
ለአምስት ወራት በሚቆየው በዚህ የወዳጅነት የስፖርት ውድድር የቴክኖሎጂ ግሩፑን ኩባንያዎች ጨምሮ ፖልሪዬስ፣ ዳሽን ባንክ፣ ኢትዮ ቴሌኮም ደቡብ ምዕራብ ዞን፣ ናሽናል ሞተርስ፣ ሞሐ ለስላሳ መጠጥ ኢንዱስትሪ፣ አዲስ ኬተሪንግ፣ ሸራተን አዲስ፣ ኒያላ ኢንሹራንስ፣ ሆራይዘን አዲስ ጐማ፣ ኢኳቶሪያል ቢዝነስ ግሩፕና ሜፖ ተካፋይ ይሆናሉ፡፡
ስፖርታዊ ውድድሮቹ በእግር ኳስ፣ በመረብ ኳስ፣ በገመድ ጉተታ፣ በሜዳ ቴኒስ፣ በሩጫ፣ በዱላ ቅብብሎሽ፣ በጠረጴዛ ቴኒስ፣ በቼዝና በዳማ የሚካሄዱ ሲሆኑ ወንዶችና ሴቶች ተወዳዳሪዎች ተሳታፊ ይሆናሉ፡፡
በስፖርት በዓሉ መክፈቻ ላይ የሚድሮክ ኢትዮጵያ ቴክኖሎጂ ግሩፕ ከፍተኛ የሥራ አመራር አባላት፣ ሠራተኞችና ቤተሰቦቻቸው እንዲሁም የተጋባዥ ተቋማት ተወካዮችና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተገኝተዋል፡፡
![]() |
![]() |
![]() |
![]() |
![]() |
![]() |
![]() |
![]() |