ለሚድሮክ ቴክኖሎጂ ግሩፕ ሠራተኞችና ኩባንያዎች የምሥጋና ፕሮግራም ተካሄደ
መጋቢት 11 ቀን 2009 ዓ.ም
* ፕሮግራሙ የተዘጋጀው በወልድያ ከተማ ለተገነባው ስታዲየምና የወጣቶች ማዕከል ምረቃ መብቃት ተሳትፎ ያደረጉትን ለማመስገን ነው
![]() |
ዶ/ር አረጋ ይርዳው የሚድሮክ ቴክኖሎጂ ግሩፕ ቺፍ ኤግዚኪዩቲቭ ኦፊሰር በምሥጋና ፕሮግራሙ ላይ |
በወልድያ ከተማ ለተገነባው የ‹‹ሙሐመድ ሁሴን አሊ አል-አሙዲ ስታዲየም›› እና የወጣቶች ማዕከል ግንባታና የምረቃ ሥነ-ሥርዓት ዝግጅት ላይ ተሳታፊ ለነበሩ የሚድሮክ ቴክኖሎጂ ግሩፕ ሠራተኞችና ካምፓኒዎች ልዩ የምሥጋና ፕሮግራም የሚድሮክ ቴክኖሎጂ ግሩፕ ቺፍ ኤግዚኪዩቲቭ ኦፊሰር ዶ/ር አረጋ ይርዳው በተገኙበት እሁድ መጋቢት 10 ቀን 2009 ዓ.ም በሸራተን አዲስ ተካሂዷል፡፡
በዚሁ የምሥጋና ሥነ-ሥርዓት ላይ ወ/ሮ ዕፅሕይወት ድንቁ የትራንስፖርቴሽን ግሩፕ እና ኮርፖሬት ማርኬቲንግ ፕሪንሲፓል ኦፕሬሽን ኦፊሰር ጥር 6 ቀን 2009 ዓ.ም በወልድያ መቻሬ ሜዳ የተካሄደውን የሙሐመድ ሁሴን አሊ አል-አሙዲ ስታዲየምና የወጣቶች ማዕከል የምረቃ ሥነ-ሥርዓት አካሔድ በተመለከተ ሪፖርት አቅርበዋል፡፡
በዕለቱ የሚድሮክ ቴክኖሎጂ ግሩፕ ቺፍ ኤግዚኪዩቲቭ ኦፊሰር ዶ/ር አረጋ ይርዳው የስታዲየሙና የወጣቶች ማዕከሉ ግንባታ ተጠናቆ ለምረቃ እንዲበቃ የቴክኖሎጂ ግሩፑ ሠራተኞች ላደረጉት ተሳትፎ ደስታቸውን ‹‹አመሰግናለሁ›› በሚል ቃል ገልጸዋል፡፡
በፕሮግራሙ ላይ ለወልድያ ስታዲየምና የወጣቶች ማዕከል ግንባታና ምረቃ ሥነ-ሥርዓት ዝግጅት መሳካት ተሳትፎ ላደረጉ የሰርተፊኬት እና ልዩ ስጦታ ከቺፍ ኤግዚኪዩቲቭ ኦፊሰር ዶ/ር አረጋ ይርዳው ተበርክቶላቸዋል፡፡
በዚሁ የምሥጋና ፕሮግራም ላይ የሚድሮክ ቴክኖሎጂ ግሩፕ ኩባንያዎች ማኔጅመንት አመራር አባላትና ሠራተኞች እንዲሁም ሌሎች ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተገኝተዋል፡፡
![]() |
ወ/ሮ ዕፅሕይወት ድንቁ ሪፖርት ሲያቀርቡ |