የሚድሮክ ቴክኖሎጂ ግሩፕ ኩባንያዎች አባል የሆኑ አምስት ኩባንያዎች በ14ኛው ኢትዮ-ኮን 2010 ዓለም አቀፍ የኮንስትራክሽን ኤግዚቪሽን ተሳታፊ ሆኑ
መስከረም 19 ቀን 2010 ዓ.ም.
![]() |
የሚድሮክ ቴክኖሎጂ ግሩፕ ስታንድ በዕለቱ የክብር እንግዳ ሲጐበኝ |
የኢትዮጵያ የኮንስትራክሽን ሥራ ተቋራጮች ማኀበር ለ14ኛ ጊዜ በአዲስ አበባ ኤግዚቪሽን ማዕከል ባዘጋጀው ኢትዮ-ኮን 2010 ዓለም አቀፍ የኮንስትራክሽን ኤግዚቪሽን ላይ የሚድሮክ ቴክኖሎጂ ግሩፕ አባል ከሆኑት ኩባንያዎች መካከል ኮምቦልቻ የብረታ ብረት ኢንዱስትሪ (ኮስፒ) ኃ.የተ.የግ.ማኀበር፣ ዘመናዊ የሕንጻ ኢንዱስትሪ (ኤም.ቢ.አይ) ኃ.የተ.የግ. ማኀበር፣ ዋንዛ ፈርኒሺንግስ ኢንዱስትሪ (ዋንዛ) ኃ.የተ.የግ. ማኀበር፣ ቪዥን አሉሚነም ኃ.የተ.የግ. ማኀበር እና አዲስ ሆም ዴፖ ኃ.የተ.የግ.ማኀበር ታሳታፊ ሆነዋል፡፡
‹‹የተሻለ ኮንስትራክሽን ለተሻለች ኢትዮጵያ›› Better Construction for Best Ethiopia” በሚል መሪ ቃል በደማቅ ሁኔታ ለአራት ቀን ሲካሄድ የቆየውን ይህንኑ ዓለም አቀፍ ኤግዚቪሽን ከሀገር የሚድሮክ ቴክኖሎጂ ግሩፕ ኩባንያዎች አባል የሆኑት አምስት ኩባንያዎች ጨምሮ 108 የሀገር ውስጥ እና ከወጪ ደግሞ 50 ድርጅቶች ተካፋይ ሆነዋል፡፡
ከመስከረም 10 እስከ 14 ቀን 2010 ዓ.ም. ድረስ የቆየውን ኢትዮ-ኮን 2010 ዓለም አቀፍ ኤግዚቪሽን መርቀው የከፈቱት የዕለቱ የክብር እንግዳ ኢንጂነር ኃ/መስቀል ተፈራ የኢትዮጵያ ኮንስትራክሽን ሥራዎች ኮርፖሬሽን ዋና ሥራ አስፈጻሚ ናቸው፡፡