የቴክኖሎጂ ግሩፑ ሠራተኞች በ2006 ታላቁ ሩጫ ላይ ተሳተፉ
ኅዳር 16 ቀን 2006 ዓ.ም.
የሚድሮክ ኢትዮጵያ ቴክኖሎጂ ግሩፕ ኩባንያዎች ሠራተኞች መነሻና መድረሻውን ጃንሜዳ ባደረገው የ2006 ዓ.ም. ታላቁ ሩጫ ላይ ተሳተፉ፡፡
ከየኩባንያዎቹ የተውጣጡ ከሁለት መቶ በላይ የሚሆኑት ሠራተኞች ህዳር 15 ቀን 2006 ዓ.ም. በሸራተን አዲስ በመሰባሰብ የፎቶግራፍ ፕሮግራም ካከናወኑ በኋላ በተዘጋጀላቸው ትራንስፖርት ወደ ጃንሜዳ በማምራት በሩጫው ላይ ተካፋይ ሆነዋል፡፡
በዕለቱ ለቴክኖሎጂ ግሩፑ ሠራተኞች የሚድሮክ ኢትዮጵያ ቺፍ ኤግዚኪዩቲቭ ኦፊሠር ዶ/ር አረጋ ይርዳውን በመወከል የእንኳን ደህና መጣችሁ አቀባበል ያደረጉት የሚድሮክ ሲኢኦ ምክትል ፕሬዚዳንት አቶ ለገሰ ተ/ማሪያም፣ የሚድሮክ ሲኢኦ ፕሪንሲፓል ኦፕሬሽን ኦፊሠር ሰብ ግሩፕ ኤ ኃላፊ አቶ ጌታቸው ሀጎስ እና አቶ ዘለቀ መንግስቴ በሲኢኦ ቢሮ የፕሪንሲፓል ኦፕሬሽን ኦፊሠር ሰብ ግሩፕ ሲ ኃላፊ ናቸው፡፡
ይህ የሩጫ ውድድር ለ13ኛ ጊዜ መካሄዱ ታውቋል፡፡
![]() |