የቺፍ ኤግዚኪዩቲቭ ቢሮ የተመሠረተበት 14ኛ ዓመት ተከበረ
ሰኔ 23 ቀን 2006 ዓ.ም.
![]() |
ዶ/ር አረጋ ይርዳው በበዓሉ ላይ ንግግር ሲያደርጉ |
የሚድሮክ ኢትዮጵያ ቴክኖሎጂ ግሩፕ ቺፍ ኤግዚኪዩቲቭ ቢሮ የተመሠረተበት 14ኛ ዓመት በዓል ሰኔ 19 ቀን 2006 ዓ.ም በመቻሬ ኮርፖሬት ሴንተር የስብሰባ ማዕከል ተከበረ፡፡
በዓሉን በማስመልከት የተዘጋጀውን ኬክ የቆረሱትና ንግግር ያደረጉት የሚድሮክ ኢትዮጵያ ቺፍ ኤግዚኪዩቲቭ ኦፊሰር ዶ/ር አረጋ ይርዳው ቢሮው ሲመሠረት የነበረውን ሁኔታ በስፋት የዳሰሱ ሲሆን፤ ላለፉት 14 ዓመታት ኩባንያዎቹን አሁን ያሉበት የዕድገት ደረጃ ላይ ለማድረስና ቁጥራቸውን ወደ 20 ለማሳደግ የተካሄደውን ከባድ ውጣ ውረድ ዘርዝረዋል፡፡
ዶ/ር አረጋ አያይዘውም ቁጥራቸው አምስት የነበሩት ኩባንያዎች አድገውና ተስፋፍተው ከስድስት ሺህ በላይ ለሆኑ ሠራተኞች የሥራ ዕድል በመፍጠራቸው መደሰታቸውን ገልፀው፤ በቀጣይም የሥራና የልማት መስኮች እየታዩ የማስፋፋት ሥራ እንደሚሰራ ተናግረዋል፡፡
![]() |
ከበዓሉ ተሳታፊዎች በከፊል |